tg-me.com/yebezdebdabewoch/1851
Last Update:
የሆነ ጊዜ አለ የሆነ ሰአት ... ማድረግ የፈለግነውን ማድረግ ሲያቅተን ፣ ሀሳባችን ከኑሯችን የተገላቢጦሽ ሲሆን ፣ ብዙ ተስፋ ስናደርግና ተስፋ መቁረጥ በኛ ላይ ተስፋ ሲቆርጥ ፣ ሀዘን በኛዉ ነግሶ በኛዉ ይደሰታል፣ ደስታ በኛ ይከፋል፣ ህልማችን ልባችን ዉስጥ እንጂ እዉኑ አለም ዉስጥ እንደሌለ ስናዉቅ ጉልበት ይከዳናል ፣አቅም ያንሰናል ፣ለምንወዳቸዉ የሚወዱትን ማድረግ አለመቻላችን ከራሳችንም ከምንወዳቸዉም ከፈጣሪም ያጣላናል ፡፡ መጥፎ ጊዜ ነዉ ራስንም ሰዉንም ማጣት ከደስታም ከእርዝቅም ያጣ መሆን፡፡ ይገባኛል ስሜትህ !!! ግን ያልፋል እመነኝ የኔ አለም ልብህ ዉስጥ ያለዉን ሀሳብ በእውንህ ታየዋለህ ፡፡ ነገር ግን ያ ጊዜ እስኪመጣ በዚህ መልኩ አትቀጥል ፍቅሬ ለተሻለ ነገ ስትል ከተሻለ ስራ ይልቅ የተሻለ ማንነት የተሻለ ስብዕና ፍጠር ፡፡ ነገሮች ከማግኘት ና ከማጣት ጋር የተገናኙበት ዘመን ላይ ብንደርስም በቁጥር የማይተመኑ ስሜቶችን ገንዘብ ሊያጠፋቸዉ እንደማይችል እመን! ባጣህበትም በምታገኝበትም ግዜ ደስተኛ ሁን 😘አንተን የሚተካ አንድም ፍጥረት የለምና 🥰
@yebezdebdabewoch
comment👉 @DayeBT
BY የቤዝ ደብዳቤዎች✍💕💌
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/yebezdebdabewoch/1851